ደረጃ 1 ሀ
የSR 509 ማጠናቀቂያ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ደረጃ በሲታክ ውስጥ አዲስ SR 99 ድልድይ ከሊንክ ቀላል ባቡር ከፍ ያለ መሪ መንገድ በታች እና ከ SR 509 መንገድ በላይ ገነባ። SR 99 ድልድይ በጁላይ 2022 ለትራፊክ ክፍት ሆነ።
ደረጃ 1 ለ
ይህ አሁን በሂደት ላይ ያለው የSR 509 ማጠናቀቂያ ፕሮጀክት፥ በI-5 እና 24th Avenue South መካከል የአዲሱን የሚያስከፍል የፍጥነት መንገድ የመጀመሪያ ማይል፥ አዳዲስ I-5 መግቢያና መውጫ መንገዶች፥ አዳዲስ መገናኛዎች፥ በI-5 ሥር አዲስ መሿለኪያ እና አዲስ South 216th Street ድልድይ ይሠራል። የፕሮጄክት ፎቶዎች እና ምስሎች በ Flickr ገጻችን እና በSR 509 የፍጥነት መንገድ መስተጋብራዊ ካርታ ላይ ይገኛሉ።
የአዲሱ የ SR 509 የፍጥነት መንገድ የመጀመሪያው ማይል እና የI-5 መገናኛዎች በSR 509 ደረጃ 1ለ ውል መሠረት ነው የሚገነቡት።
የፕዩጀት ሳውንድ ጌትዌይ ፕሮግራም ምንድነው?
የPuget Sound Gateway Program በደቡብ ኪንግ ካውንቲ ውስጥ የSR 509 ማጠናቀቂያ ፕሮጄክትን እና በፒርስ ካውንቲ ውስጥ የSR 167 ማጠናቀቂያ ፕሮጄክትን ያካትታል። እነዚህ ማሻሻያዎች አንድ ላይ ሆነው የስቴቱን ትላልቅ ወደቦች በኪንግ እና ፒርስ ካውንቲዎች ውስጥ ካሉ ከቁልፍ ማከፋፈያ ማዕከሎች ጋር በማገናኘት የስቴቱን ኢኮኖሚያዊ ተወዳዳሪነት፥ በብሔራዊም ሆነ በዓለማቀፍ ደረጃ ያሳድጋሉ።