Skip to main content
WSDOT online open houses

የምኖረው፥ የምሠራው ወይም የምጓዘው በኬንት ውስጥ ነው

ወደ ደቡብ ሂያጅ I-5 ከ SR 516 እና South 272nd Street መካከል

WSDOT ትራፊክ በ SR 509 እና I-5 መካከል ሲሸጋገር እንዲረዳ በ I-5 ላይ ማሻሻያዎች እያደረገ ነው በ SR 516 እና South 272nd Street መካከል አዲስ ወደ ደቡብ ወሳጅ መስመር ከSR 509 ወደ ኬንት ቫሊ እና ፌዴራል ዌይ ለሚጓዝ ትራፊክ I-5 አቅም ይጨምራል። ሠራተኞች ሥራ ይጀምራሉ ተብሎ የሚጠበቀው ክረምት 2024 ላይ ነው።

ወደ ደቡብ ወሳጅ I-5ን የሚጠቀሙ ከሆነ፥ በርካታ የጥግ መስመር መዘጋት እና በየጊዜው የማታ እና የቅዳሜና እሁድ የመስመር መዘጋቶች ይጠብቁ።  ሁሉም የግንባታ ሥራ የሚካሄደው ከጊዜያዊ ሲሚንቶ ማገጃዎች ኋላ ሲሆን፥ ተጓዥ ሕዝብ ግን ሁልጊዜ በሥራ ዞኖች ሲያልፍ ዝግ ማለት እና ከሥራ ቦታዎቹ የሚገቡና የሚወጡ ጭነት መኪናዎችን ማስተዋል አለባቸው።

South 259th Street አጠገብ McSorley Creek

ከ South 272nd Street በስተሰሜን በሚገኘው በ McSorley Creek በI-5 ስር ያለ ቦይ የውሃውን ፍሰት ለመጠበቅ እና I-5ን የመቋቋም አቅም እንዲኖረው በትልቁ ቦይ ይተካል። ሠራተኞቹ የግንባታ ቦታው ጋር የሚገቡት በSouth 259th Street በኩል ነው።

South 259th Street አጠገብ የሚኖሩ ወይም በሱ በኩል የሚጓዙ ከሆነ፥ በዚህ ቦታ ላይ የግንባታ ትራፊክ እና በየጊዜው የመስመር እና የጥግ መስመር መዘጋት ይጠብቁ።

የማክሶርሊ ክሪክ ቦይ እና I-5 ረዳት መስመር አተረጓጎም

የድምጽ መከላከያ ግድግዳ ማራዘሚያ

WSDOT በኬንት ውስጥ ከ 32nd Place South በስተምስራቅ ወደ ሰሜን ያለውን የድምጽ መከላከያ ግድግዳ በ230 ጫማ ያራዝመዋል። ለዚህ የግንባታ የጊዜ ሠሌዳ ገና አልተዘጋጀም።

አዲስ የታቀደ የድምጽ ግድግዳ ከላይ እይታ።
የጩኸት ግድግዳ ወደ ሰሜን አቅጣጫ I-5 መስመሮች እና በኬንት 32ኛ ቦታ ደቡብ

32nd Place South አጠገብ የታቀደው የድምጽ መከላከያ ግድግዳ ጎን ከሆነ የሚኖሩት፥ ግንባታው ከመጀመሩ በፊት የዳሰሳ ሠራተኞች እንዲያነጋግሩዎት መጠበቅ አለብዎት። በግንባታው ወቅት ሠራተኞች አፈሩን ለመጠቅጠቅ፣ ለድምፅ ግድግዳ መሠረት የሚሆን ሲሚንቶ ለማፍሰስ እና አዳዲስ የሲሚንቶ ፓነሎችን ለመቅረጽ ከባባድ መሣሪያዎች ይጠቀማሉ።

ተቋራጮች የአካባቢ የድምፅ ፈቃዶችን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል እና ጫጫታ እና ሊረብሽ የሚችል የግንባታ እንቅስቃሴን ለመቀነስ እርምጃዎችን ይወስዳሉ። በጎረቤቶች እና ንግዶች አቅራቢያ ጫጫታ እና ግንባታን ለመቆጣጠር ምርጥ አሠራሮች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

ጥያቄዎች ወይም ሐሳቦች?

ስለ ግንባታው ጥያቄ ወይም ሐሳብ ካልዎት በማንኛውም ጊዜ ቡድናችንን በ24 ሰዓት የስልክ መስመር፥ በ206-225-0674 ወይም በSR509Construction@wsdot.wa.gov ማግኘት ይችላሉ።