Skip to main content

የምኖረው፥ የምሠራው ወይም የምጓዘው በብዩሪየን በኩል ነው

South 160th Street

በትራፊክ አካሄዶች ላይ ለውጦችን ለማስተናገድ እና ደህንነትን ለማሻሻል፣ WSDOT አደባባዮችን በመጨመር የSR 509/South 160th Street መገናኛን እንደገና ይገነባል።

የ SR 509/ደቡብ 160ኛ ስትሪት መለወጫ
SR 509/ደቡብ 160ኛ ስትሪት መለወጫ ንድፍ

በSR 509/South 160th Street መገናኛ አካባቢ የሚኖሩ፥ የሚሠሩ ወይም የሚጓዙ ከሆነ ድምጽ፥ አቧራ እና በተለምዶ ከመንገድ ግንባታ ጋር የተያያዘ የትራፊክ አካሄድ ለውጥ ይጠብቁ።

የSR 509/South 160th Street ግንባታ የጀመረው 2024 በጋ ላይ ሲሆን በውሃ ፍሳሽ ግንባታ ነበር የጀመረው። የSR 509/South 160th Street መገናኛ ሥራ የSouth 160th Street ቅዳሜ እና እሁድ እንዲዘጋ ያስገድዳል። የመዘጊያ ቀኖች ከተወሰኑ በኋላ ተጨማሪ መረጃ እናጋራለን። ለንግድ ቤቶች እና መኖሪያ ቤቶች የአካባቢ ተደራሽነት ይጠበቃል።

አደባባዮች

ጥናቶች እንደሚያሳዩት አደባባዩዎች ከባህላዊ የማቆሚያ ምልክት ወይም የትራፊክ ምልክት ቁጥጥር ከሚደረግባቸው መገናኛዎች የበለጠ ደህንነታቸው የተጠበቀ ነው። እንደ እግረኛ፣ ብስክሌት ነጂ ወይም ሹፌር ሆነው በአደባባዩ ውስጥ እንዴት እንደሚጓዙ የበለጠ ለማወቅ የWSDOTን አደባባይ የትራፊክ ደህንነት ድረ-ገጽ ይመልከቱ።

ድምጽ መከላከያ ግድግዳዎች

ከSR 509/South 160th Street መገናኛ በደቡብ ምዕራብ በኩል፥ ወደ ደቡብ አቅጣጫ ከሚወስደው SR 509 መግቢያ ጎን አንድ የድምጽ መከላከያ ግድግዳ ይገነባል። ሁለተኛው የድምጽ መከላከያ ግድግዳ የሚገነባው በSR 509/South 160th Street መገናኛ ሰሜን ምስራቅ በኩል በ Fourth Avenue South እና በሰሜን አቅጣጫ SR 509 መካከል ነው።

በS 160th Street እና SR 509 መገናኛ ላይ ያለ አደባባዩ የአየር ላይ እይታ። ሁለት የታቀዱ የድምፅ ግድግዳዎች በSR 509 በብርቱካን ምልክት ተደርገዋል።
ደቡብ 160ኛ ስትሪት/SR 509 የመቀያየር ንድፍ

በSR 509/South 160th Street መገናኛ ዙሪያ ከታቀዱት የድምጽ መከላከያ ግድግዳዎች በአንዱ አጠገብ የሚኖሩ ከሆነ ግንባታው ከመጀመሩ በፊት የዳሰሳ ጥናት ሰራተኞች እርስዎን እንዲያገኙ መጠበቅ አለብዎት። በግንባታው ወቅት ሠራተኞቹ የድምጽ መከላከያ ግድግዳ መሠረቶችን ለመቆፈር፣ አፈሩን ለመጠቅጠቅ፣ ለድምፅ ግድግዳ መሠረት የሚሆን ሲሚንቶ ለማፍሰስ እና አዳዲስ የሲሚንቶ ፓነሎችን ለመትከል ከባባድ መሣሪያዎች ይጠቀማሉ። የድምጽ መከላከያ ግድግዳው ግንባታ እንደየቦታው ሁኔታ ከስድስት እስከ ዘጠኝ ወራት ይፈጃል ተብሎ ይጠበቃል።

የተጠናቀቀ የድምፅ ግድግዳ ምስል.
በSR 509 ማጠናቀቂያ ፕሮጄክት ደረጃ 1ለ ላይ የፕሮጄክቱ ቡድን ያጠናቀቀው የድምጽ መከላከያ ግድግዳ

ተቋራጮች የአካባቢ የድምፅ ፈቃዶችን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል እና ጫጫታ እና ሊረብሽ የሚችል የግንባታ እንቅስቃሴን ለመቀነስ እርምጃዎችን ይወስዳሉ። በጎረቤቶች እና ንግዶች አቅራቢያ ጫጫታ እና ግንባታን ለመቆጣጠር ምርጥ አሠራሮች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

  • ጫጫታ ካለው የምሽት ስራ በፊት በአቅራቢያው ለሚገኙ ነዋሪዎች ማስታወቂያ መስጠት።
  • አቧራ ለመከላከል መሬቱን ማርጠብ።
  • ቁሳቁሶችን ሲጣሉ እና የኋላ በር ሲዘጋ ድምጽ ለመገደብ የከባድ መኪና ንጣፎች።

ጥያቄዎች ወይም ሐሳቦች?

ስለ ግንባታው ጥያቄ ወይም ሐሳብ ካልዎት በማንኛውም ጊዜ ቡድናችንን በ24 ሰዓት የስልክ መስመር፥ በ206-225-0674 ወይም በSR509Construction@wsdot.wa.gov ማግኘት ይችላሉ።