Skip to main content

የምኖረው፥ የምሠራው ወይም የምጓዘው በዴሞይንስ፥ ሲታክ እና ደቡብ ብዩሪየን በኩል ነው።

Des Moines Memorial Drive/South 188th Street

አዲሱ የSR 509/South 188th Street መገናኛ አሁን ወደ ሁሉም የጉዞ አቅጣጫዎች መግቢያ ይኖረዋል። ይህን የትራፊክ ሂደት ለውጥ ለማስተናገድ እና ደህንነትን ለማሻሻል፥ WSDOT አደባባዮች በመጨመር መገናኛውን በድጋሚ ይገነባዋል። ወደ ደቡብ ለሚሄድ የSR 509 ትራፊክ፥ የSouth 188th Street መገናኛ ወደሚከፈልበት የፍጥነት መንገድ ክፍል ከመቀጠልዎ በፊት የመጨረሻው መውጫ ይሆናል። 

የ SR 509/ደቡብ 188ኛ ስትሪት መለወጫ

አዳዲስ የሥራ ዞኖች ለመፍጠር ጊዜያዊ መውጫ/መግቢያዎችን በመሥራት፥ ሠራተኞች በዚህ ቦታ ላይ የግንባታ ሥራ እንጀምራለን ብለው የሚጠብቁት ከ2025 በጋ ጀምሮ ነው። በSR 509/South 160th Street መገናኛ አካባቢ የሚኖሩ፥ የሚሠሩ ወይም የሚጓዙ ከሆነ ድምጽ፥ አቧራ እና በተለምዶ ከመንገድ ግንባታ ጋር የተያያዘ የትራፊክ አካሄድ ለውጥ ይጠብቁ። ለንግድ ቤቶች የአካባቢ ተደራሽነት ይጠበቃል።

አዲስ SR 509 የፍጥነት መንገድ

አዲሱ የ SR 509 የፍጥነት መንገድ በ24th Avenue South አጠገብ ያለው አዲሱ የ SR 509 የፍጥነት መንገድ ክፍል ጋር  ከመገናኘቱ በፊት South 188th Street መገናኛ ወደ ደቡብ ይቀጥልና፣ በLake to Sound Trail ላይ አልፎ፥ ከSouth 192nd Street ሥር፣ በDes Moines Memorial Drive ላይ፣ እና በSouth 200th Street እና Des Moines Creek Park በላይ ያልፋል።

የ Lake to Sound መንገድን የሚጠቀሙ ከሆነ፦ መንገዱ በግንባታ ወቅት ባብዛኛው ክፍት ሆኖ ይቆያል። የድልድይ መጋጠሚያዎችን ለማስገባት ወይም የግንባታ መሣሪያ መንገዱን እንዲሻገር ለማስቻል ሠራተኞች መንገዱን ሊዘጉ ይችላሉ። በእነዚህ ጊዜያት የመንገድ ተጠቃሚዎችን ለመምራት ጠቋሚዎች እና የትራፊክ መቆጣጠሪያ እርምጃዎች ይኖራሉ። በተለምዶ ከግንባታ እና ከከባድ መሣሪያ የሚመጣ ድምጽ ይኖራል በለው ይጠብቁ።

192nd Streetን የሚጠቀሙ ከሆነ፦ የወደፊቱ SR 509 የፍጥነት መንገድ በሥሩ የሚያልፍበት አዲስ የ South 192nd Street ድልድይ ሠራተኞች በሚሠሩበት ጊዜ፥ መንገዱ ከ2025 ጀምሮ ለትራፊክ በሙሉ ለዘጠኝ ወራት ዝግ ይሆናል። የመጨረሻ የSouth 192nd Street ድልድይ ግንባታ የጊዜ ሠሌዳ ሲኖረን፥ ይህን መዘጋት የማህበረሰብ አባላት መቼ መጠበቅ እንደሚችሉ ተጨማሪ መረጃ እናጋራለን።

South 194th Street ን የሚጠቀሙ ከሆነ፦ ከ Des Moines Memorial Drive ጋር ያለው የ South 194th Street ግንኙነት በቋሚነት ይዘጋል። ይህ መዘጋት የሚከሰተው የSouth 192nd Street ድልድይ ከተጠናቀቀ እና ለተጓዦች ክፍት ከሆነ በኋላ ነው።

South 194th Street አጠገብ የሚኖሩ ከሆነ፦ አዲሱ የ SR 509 የፍጥነት መንገድ በዚህ ቦታ ላይ ያልፋል። አብዛኛው ሥራ የሚካሄደው ቀን ሲሆን፥ አንዳንድ የማታ ግንባታዎች እንዳስፈላጊነቱ ይዘጋጃሉ። በተለምዶ ከከባድ ግንባታ ጋር የተያያዙ አንዳንድ የቀን ድምጽ እና አቧራ ይጠብቁ።

የ SR 509/ደቡብ 192ኛ ጎዳና

በ South 200th Street እና South 192nd Street መካከል Des Moines Memorial Driveን የሚጠቀሙ ከሆነ፦ የድልድይ መጋጠሚያዎችን ለማስገባት እና ሌሎች የግንባታ እንቅስቃሴዎችን ለማከናወን አንዳንድ የማታ መዘጋቶች ይዘጋጃሉ።

የ SR 509/Des Moines Memorial Drive መሻገሪያ አቀራረብ

Des Moines Creek Trail ን የሚጠቀሙ ከሆነ፦  የድልድይ መጋጠሚያዎችን ለማስገባት ወይም የግንባታ መሣሪያ መንገዱን እንዲሻገር ለማስቻል ሠራተኞች መንገዱን ሊዘጉ ይችላሉ። በእነዚህ ጊዜያት የመንገድ ተጠቃሚዎችን ለመምራት ጠቋሚዎች እና የትራፊክ መቆጣጠሪያ እርምጃዎች ይኖራሉ። በተለምዶ ከግንባታ እና ከከባድ መሣሪያ ጋር የሚገናኝ ድምጽ ይጠብቁ።

South 200th Street ን የሚጠቀሙ ከሆነ፦ South 200th Street ቀን በግንባታው ጊዜ ክፍት ሆኖ ይቆያል እና ወደ ሌላ አቅጣጫ እንዲዞር አይደረግም። ከፍ ያለውን የፍጥነት መንገድ ለመገንባት በርካታ የማታ መዘጋቶች ይኖራሉ።

የ SR 509/ደቡብ 200ኛ መንገድ ማቋረጫ

SR 509 የፍጥነት መንገድ መስተጋብራዊ ካርታን በመጎብኘት WSDOT በእያንዳቸው በእነዚህ ቦታዎች ምን እንዳቀደ የበለጠ ማወቅ ይችላሉ።

ተቋራጮች የአካባቢ የድምፅ ፈቃዶችን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል እና ጫጫታ እና ሊረብሽ የሚችል የግንባታ እንቅስቃሴን ለመቀነስ እርምጃዎችን ይወስዳሉ። በጎረቤቶች እና ንግዶች አቅራቢያ ጫጫታ እና ግንባታን ለመቆጣጠር ምርጥ አሠራሮች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

  • ጫጫታ ካለው የምሽት ስራ በፊት በአቅራቢያው ለሚገኙ ነዋሪዎች ማስታወቂያ መስጠት።
  • አቧራ ለመከላከል መሬቱን ማርጠብ።
  • ቁሳቁሶችን ሲጣሉ እና የኋላ በር ሲዘጋ ድምጽ ለመገደብ የከባድ መኪና ንጣፎች።

ጥያቄዎች ወይም ሐሳቦች?

ስለ ግንባታው ጥያቄ ወይም ሐሳብ ካልዎት በማንኛውም ጊዜ ቡድናችንን በ24 ሰዓት የስልክ መስመር፥ በ206-225-0674 ወይም በSR509Construction@wsdot.wa.gov ማግኘት ይችላሉ።