ከ SR 509/24th Avenue South ወደ South 188th Street አዲስ የፍጥነት መንገድ

Share ከ SR 509/24th Avenue South ወደ South 188th Street አዲስ የፍጥነት መንገድ on Facebook Share ከ SR 509/24th Avenue South ወደ South 188th Street አዲስ የፍጥነት መንገድ on Twitter Share ከ SR 509/24th Avenue South ወደ South 188th Street አዲስ የፍጥነት መንገድ on Linkedin Email ከ SR 509/24th Avenue South ወደ South 188th Street አዲስ የፍጥነት መንገድ link

እንኳን ደህና መጡ

WSDOT ከState Route 509/24th Avenue South ወደ South 188th Street አዲስ የፍጥነት መንገድ ፕሮጀክት በ2024 ግንባታ ይጀምራል። ይህ ፕሮጄክት የSR 509 ማጠናቀቂያ ፕሮጄክት የመጨረሻ፥ ሙሉ በሙሉ በገንዘብ የተደገፈ ደረጃ (ደረጃ 2) ነው።

እንዴት እንደሚሳተፉ

ይህ የመስመር ላይ የጉብኝት ክፍለ ጊዜ የፕሮጄክት ግንባታ ሥራ ስለሚከናወኑባቸው ቦታዎች እና የፕሮጄክቱን ከሁሉም በላይ የሚታዩትን ተግባራት ለማጠናቀቅ የጊዜ ሠሌዳዎችን ያቀርባል። እባክዎ ስለ ፕሮጄክቱ የበለጠ ለማወቅ የሚከተሉትን ገጾች ይጎብኙ እና ጥያቄዎችዎን በ አትጥፉ ገጽ ላይ ያካፍሉ።

የመስመር ላይ የጉብኝት ክፍለ ጊዜን እስከ ኦክቶበር 25፥ 2024 ድረስ ማግኘት ይችላሉ።

የፕሮጀክት አጠቃላይ እይታ

የSR 509/24th Avenue South እስከ South 188th Street አዲስ የፍጥነት መንገድ ፕሮጄክት የSR 509 ማጠናቀቂያ ፕሮጄክት ማሻሻያዎች የመጨረሻው ደረጃ ሲሆን፥ ይህም በሲታክ ውስጥ SR 509ን ከI-5 ጋር ያገናኛል። ፕሮጄክቱ በ2028 ከተጠናቀቀ በኋላ፥ በቦታው አልፈው የሚጓዙ ሰዎች በI-5፣ ሲታክ አየር ማረፊያ፣ በፖርት ኦፍ ሲያትል እና በደቡብ ኪንግ ካውንቲ የህዝብ ማእከላት መካከል ሲጓዙ SR 518 እና የአካባቢ መንገዶችን ባቋራጭ ማለፍ ይችላሉ። የጭነት አሽከርካሪዎች መድረሻቸው ጋር ለመድረስ አዲስ መንገድ ስለሚጠቀሙ የማህበረሰብ አባላት በአካባቢው መንገዶች ላይ ያነሰ የጭነት መኪኖች ያያሉ። አዲሱ የSR 509 ክፍል የክፍያ ቶል ይኖረዋል። በግንባታው ወቅት እና ከተጠናቀቀ በኋላ ሰዎች አሁን ያሏቸውን ወደ SR 509 እና ወደ I-5 መግቢያ ቦታዎች መጠቀም መቀጠል ይችላሉ፥ እንዲሁም ሰዎች ዛሬ በሚጠቀሟቸው መንገዶች ላይ ቶል መክፈል አያስፈልጋቸውም።

በፕሮጄክቱ ውስጥ ምን ይካተታል?

የSR 509/24th Avenue South እስከ South 188th Street አዲስ የፍጥነት መንገድ ፕሮጄክት የሚከተሉትን ያካትታል፦

  • ከሁለት አዲስ ማይሎች በላይ የፍጥነት መንገድ።
  • ወደ ደቡብ አቅጣጫ I-5 ላይ በኬንት ውስጥ በSR 516 እና South 272nd Street መካከል አንድ ተጨማሪ መስመር።
  • ብዩሪየን ውስጥ South 160th Street ላይ እና ሲታክ ውስጥ South 188th Street ላይ አደባባዮች።
  • አዲስ ድምጽ መከላከያ ግድግዳዎች።
  • በፕሮጄክቱ ኮሪደር ውስጥ የተፈጥሮ ቦታዎችን ወደነበሩበት መመለስ።

የፕሮጄክት የጊዜ ሠሌዳ

የግንባታ ሥራዎች ጅምር ላይ በፕሮጀክቱ አካባቢ በሙሉ የእፅዋት ማንሳትን ያካትታሉ። ከበድ ያለ የግንባታ ሥራ የሚጀምረው በፎል 2024 ነው። በሚኖሩበት፣ በሚሠሩበት እና በሚጓዙበት አካባቢ ምን እንደሚጠብቁ ለማወቅ በሚቀጥሉት ገፆች ያሉትን የስራ ዞኖች ይመልከቱ።

የ SR 509 ፕሮጀክት ደረጃዎችን ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻ የሚያሳይ የጊዜ መስመር። የደረጃ 2 ግንባታ በ2024 ይጀምራል እና በ2028 ለትራፊክ ክፍት ይሆናል።

የSR 509 ማጠናቀቂያ ፕሮጄክት ከአሁኑ በግንባታ ላይ ነው። ደረጃ 1ሀ ለትራፊክ ክፍት የሆነው በ2022፣ ደረጃ 1b በ2025 ለትራፊክ ክፍት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፣ እና ደረጃ 2 በ2028 ለትራፊክ ክፍት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

መግቢያ

የግንባታ ባለሙያዎች በአራት የተለያዩ ከተሞች ውስጥ ሥራ ያከናውናሉ፦ ብዩሪየን፥ ዴሞይንስ፥ ሲታክ እና ኬንት። በአካባቢው እየተጓዙ ወይም እየኖሩ ወይም በአቅራቢያ እየሠሩ ምን እንደሚጠብቁ እንዲያውቁ ለእያንዳንዱ የግንባታ ቦታ ዝርዝሮችን አቅርበናል።

በዚያ አካባቢ ስላለው የግንባታ ዝመናዎች የበለጠ ለማወቅ ከላይ ያሉትን አራት ማዕዘኖች ወይም ከታች ያሉትን ማገናኛዎች ጠቅ ያድርጉ።

የምኖረው፥ የምሠራው ወይም የምጓዘው በብዩሪየን በኩል ነው

South 160th Street

በትራፊክ አካሄዶች ላይ ለውጦችን ለማስተናገድ እና ደህንነትን ለማሻሻል፣ WSDOT አደባባዮችን በመጨመር የSR 509/South 160th Street መገናኛን እንደገና ይገነባል።

የ SR 509/ደቡብ 160ኛ ስትሪት መለወጫSR 509/ደቡብ 160ኛ ስትሪት መለወጫ ንድፍ በSR 509/South 160th Street መገናኛ አካባቢ የሚኖሩ፥ የሚሠሩ ወይም የሚጓዙ ከሆነድምጽ፥ አቧራ እና በተለምዶ ከመንገድ ግንባታ ጋር የተያያዘ የትራፊክ አካሄድ ለውጥ ይጠብቁ።

የSR 509/South 160th Street ግንባታ የጀመረው 2024 በጋ ላይ ሲሆን በውሃ ፍሳሽ ግንባታ ነበር የጀመረው። የSR 509/South 160th Street መገናኛ ሥራ የSouth 160th Street ቅዳሜ እና እሁድ እንዲዘጋ ያስገድዳል። የመዘጊያ ቀኖች ከተወሰኑ በኋላ ተጨማሪ መረጃ እናጋራለን። ለንግድ ቤቶች እና መኖሪያ ቤቶች የአካባቢ ተደራሽነት ይጠበቃል።

አደባባዮች

ጥናቶች እንደሚያሳዩት አደባባዩዎች ከባህላዊ የማቆሚያ ምልክት ወይም የትራፊክ ምልክት ቁጥጥር ከሚደረግባቸው መገናኛዎች የበለጠ ደህንነታቸው የተጠበቀ ነው። እንደ እግረኛ፣ ብስክሌት ነጂ ወይም ሹፌር ሆነው በአደባባዩ ውስጥ እንዴት እንደሚጓዙ የበለጠ ለማወቅ የWSDOTን አደባባይ የትራፊክ ደህንነት ድረ-ገጽ ይመልከቱ።

ድምጽ መከላከያ ግድግዳዎች

ከSR 509/South 160th Street መገናኛ በደቡብ ምዕራብ በኩል፥ ወደ ደቡብ አቅጣጫ ከሚወስደው SR 509 መግቢያ ጎን አንድ የድምጽ መከላከያ ግድግዳ ይገነባል። ሁለተኛው የድምጽ መከላከያ ግድግዳ የሚገነባው በSR 509/South 160th Street መገናኛ ሰሜን ምስራቅ በኩል በ Fourth Avenue South እና በሰሜን አቅጣጫ SR 509 መካከል ነው።

በS 160th Street እና SR 509 መገናኛ ላይ ያለ አደባባዩ የአየር ላይ እይታ። ሁለት የታቀዱ የድምፅ ግድግዳዎች በSR 509 በብርቱካን ምልክት ተደርገዋል።ደቡብ 160ኛ ስትሪት/SR 509 የመቀያየር ንድፍ በSR 509/South 160th Street መገናኛ ዙሪያ ከታቀዱት የድምጽ መከላከያ ግድግዳዎች በአንዱ አጠገብ የሚኖሩ ከሆነ ግንባታው ከመጀመሩ በፊት የዳሰሳ ጥናት ሰራተኞች እርስዎን እንዲያገኙ መጠበቅ አለብዎት። በግንባታው ወቅት ሠራተኞቹ የድምጽ መከላከያ ግድግዳ መሠረቶችን ለመቆፈር፣ አፈሩን ለመጠቅጠቅ፣ ለድምፅ ግድግዳ መሠረት የሚሆን ሲሚንቶ ለማፍሰስ እና አዳዲስ የሲሚንቶ ፓነሎችን ለመትከል ከባባድ መሣሪያዎች ይጠቀማሉ። የድምጽ መከላከያ ግድግዳው ግንባታ እንደየቦታው ሁኔታ ከስድስት እስከ ዘጠኝ ወራት ይፈጃል ተብሎ ይጠበቃል።

የተጠናቀቀ የድምፅ ግድግዳ ምስል.በSR 509 ማጠናቀቂያ ፕሮጄክት ደረጃ 1ለ ላይ የፕሮጄክቱ ቡድን ያጠናቀቀው የድምጽ መከላከያ ግድግዳ

ተቋራጮች የአካባቢ የድምፅ ፈቃዶችን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል እና ጫጫታ እና ሊረብሽ የሚችል የግንባታ እንቅስቃሴን ለመቀነስ እርምጃዎችን ይወስዳሉ። በጎረቤቶች እና ንግዶች አቅራቢያ ጫጫታ እና ግንባታን ለመቆጣጠር ምርጥ አሠራሮች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

  • ጫጫታ ካለው የምሽት ስራ በፊት በአቅራቢያው ለሚገኙ ነዋሪዎች ማስታወቂያ መስጠት።
  • አቧራ ለመከላከል መሬቱን ማርጠብ።
  • ቁሳቁሶችን ሲጣሉ እና የኋላ በር ሲዘጋ ድምጽ ለመገደብ የከባድ መኪና ንጣፎች።

ጥያቄዎች ወይም ሐሳቦች?

ስለ ግንባታው ጥያቄ ወይም ሐሳብ ካልዎት በማንኛውም ጊዜ ቡድናችንን በ24 ሰዓት የስልክ መስመር፥ በ206-225-0674 ወይም በSR509Construction@wsdot.wa.gov ማግኘት ይችላሉ።

የምኖረው፥ የምሠራው ወይም የምጓዘው በዴሞይንስ፥ ሲታክ እና ደቡብ ብዩሪየን በኩል ነው።

Des Moines Memorial Drive/South 188th Street

አዲሱ የSR 509/South 188th Street መገናኛ አሁን ወደ ሁሉም የጉዞ አቅጣጫዎች መግቢያ ይኖረዋል። ይህን የትራፊክ ሂደት ለውጥ ለማስተናገድ እና ደህንነትን ለማሻሻል፥ WSDOT አደባባዮች በመጨመር መገናኛውን በድጋሚ ይገነባዋል። ወደ ደቡብ ለሚሄድ የSR 509 ትራፊክ፥ የSouth 188th Street መገናኛ ወደሚከፈልበት የፍጥነት መንገድ ክፍል ከመቀጠልዎ በፊት የመጨረሻው መውጫ ይሆናል።

የ SR 509/ደቡብ 188ኛ ስትሪት መለወጫ

አዳዲስ የሥራ ዞኖች ለመፍጠር ጊዜያዊ መውጫ/መግቢያዎችን በመሥራት፥ ሠራተኞች በዚህ ቦታ ላይ የግንባታ ሥራ እንጀምራለን ብለው የሚጠብቁት ከ2025 በጋ ጀምሮ ነው። በSR 509/South 160th Street መገናኛ አካባቢ የሚኖሩ፥ የሚሠሩ ወይም የሚጓዙ ከሆነ ድምጽ፥ አቧራ እና በተለምዶ ከመንገድ ግንባታ ጋር የተያያዘ የትራፊክ አካሄድ ለውጥ ይጠብቁ። ለንግድ ቤቶች የአካባቢ ተደራሽነት ይጠበቃል።

አዲስ SR 509 የፍጥነት መንገድ

አዲሱ የ SR 509 የፍጥነት መንገድ በ24th Avenue South አጠገብ ያለው አዲሱ የ SR 509 የፍጥነት መንገድ ክፍል ጋር ከመገናኘቱ በፊት South 188th Street መገናኛ ወደ ደቡብ ይቀጥልና፣ በLake to Sound Trail ላይ አልፎ፥ ከSouth 192nd Street ሥር፣ በDes Moines Memorial Drive ላይ፣ እና በSouth 200th Street እና Des Moines Creek Park በላይ ያልፋል።

የ Lake to Sound መንገድን የሚጠቀሙ ከሆነ፦ መንገዱ በግንባታ ወቅት ባብዛኛው ክፍት ሆኖ ይቆያል። የድልድይ መጋጠሚያዎችን ለማስገባት ወይም የግንባታ መሣሪያ መንገዱን እንዲሻገር ለማስቻል ሠራተኞች መንገዱን ሊዘጉ ይችላሉ። በእነዚህ ጊዜያት የመንገድ ተጠቃሚዎችን ለመምራት ጠቋሚዎች እና የትራፊክ መቆጣጠሪያ እርምጃዎች ይኖራሉ። በተለምዶ ከግንባታ እና ከከባድ መሣሪያ የሚመጣ ድምጽ ይኖራል በለው ይጠብቁ።

192nd Streetን የሚጠቀሙ ከሆነ፦ የወደፊቱ SR 509 የፍጥነት መንገድ በሥሩ የሚያልፍበት አዲስ የ South 192nd Street ድልድይ ሠራተኞች በሚሠሩበት ጊዜ፥ መንገዱ ከ2025 ጀምሮ ለትራፊክ በሙሉ ለዘጠኝ ወራት ዝግ ይሆናል። የመጨረሻ የSouth 192nd Street ድልድይ ግንባታ የጊዜ ሠሌዳ ሲኖረን፥ ይህን መዘጋት የማህበረሰብ አባላት መቼ መጠበቅ እንደሚችሉ ተጨማሪ መረጃ እናጋራለን።

South 194th Street ን የሚጠቀሙ ከሆነ፦ ከ Des Moines Memorial Drive ጋር ያለው የ South 194th Street ግንኙነት በቋሚነት ይዘጋል። ይህ መዘጋት የሚከሰተው የSouth 192nd Street ድልድይ ከተጠናቀቀ እና ለተጓዦች ክፍት ከሆነ በኋላ ነው።

South 194th Street አጠገብ የሚኖሩ ከሆነ፦ አዲሱ የ SR 509 የፍጥነት መንገድ በዚህ ቦታ ላይ ያልፋል። አብዛኛው ሥራ የሚካሄደው ቀን ሲሆን፥ አንዳንድ የማታ ግንባታዎች እንዳስፈላጊነቱ ይዘጋጃሉ። በተለምዶ ከከባድ ግንባታ ጋር የተያያዙ አንዳንድ የቀን ድምጽ እና አቧራ ይጠብቁ።

የ SR 509/ደቡብ 192ኛ ጎዳና

በ South 200th Street እና South 192nd Street መካከል Des Moines Memorial Driveን የሚጠቀሙ ከሆነ፦ የድልድይ መጋጠሚያዎችን ለማስገባት እና ሌሎች የግንባታ እንቅስቃሴዎችን ለማከናወን አንዳንድ የማታ መዘጋቶች ይዘጋጃሉ።

የ SR 509/Des Moines Memorial Drive መሻገሪያ አቀራረብ

Des Moines Creek Trail ን የሚጠቀሙ ከሆነ፦ የድልድይ መጋጠሚያዎችን ለማስገባት ወይም የግንባታ መሣሪያ መንገዱን እንዲሻገር ለማስቻል ሠራተኞች መንገዱን ሊዘጉ ይችላሉ። በእነዚህ ጊዜያት የመንገድ ተጠቃሚዎችን ለመምራት ጠቋሚዎች እና የትራፊክ መቆጣጠሪያ እርምጃዎች ይኖራሉ። በተለምዶ ከግንባታ እና ከከባድ መሣሪያ ጋር የሚገናኝ ድምጽ ይጠብቁ።

South 200th Street ን የሚጠቀሙ ከሆነ፦ South 200th Street ቀን በግንባታው ጊዜ ክፍት ሆኖ ይቆያል እና ወደ ሌላ አቅጣጫ እንዲዞር አይደረግም። ከፍ ያለውን የፍጥነት መንገድ ለመገንባት በርካታ የማታ መዘጋቶች ይኖራሉ።

የ SR 509/ደቡብ 200ኛ መንገድ ማቋረጫ

SR 509 የፍጥነት መንገድ መስተጋብራዊ ካርታን በመጎብኘት WSDOT በእያንዳቸው በእነዚህ ቦታዎች ምን እንዳቀደ የበለጠ ማወቅ ይችላሉ።

የምኖረው፥ የምሠራው ወይም የምጓዘው በ Barnes Creek አካባቢ ነው

Barnes Creek የረግረግ ማስተካከያ

በዴሞይንስ ውስጥ Barnes Creek ላይ ሰፊ የረግረግ ማሻሻያ ፕሮጄክት ታቅዷል ቦታው ከ Kent-Des Moines Road እስከ South 220th Street ድረስ ይሄዳል የ Barnes Creek ማደሻ ቦታ ለክልሉ ተወላጅ ተክሎች መኖሪያ አካባቢን ያሻሽላል።

የባርነስ ክሪክ ዌትላንድ ማገገሚያ ፕሮጀክት ጽንሰ ሃሳብ አተረጓጎም የሚያሳይ ካርታ። የፕሮጀክቱ ወሰን ከኬንት ዴስ ሞይንስ መንገድ ወደ ደቡብ 220ኛ ጎዳና ይዘልቃል። በተለያዩ አረንጓዴ ጥላዎች ምልክት የተደረገባቸው 4 የተለያዩ የማገገሚያ ዓይነቶች አሉ።

Barnes Creek Nature Trailን የሚጠቀሙ ከሆነ፥ ሠራተኞች በቦታው ላይ ሲሠሩ መንገዱ በየጊዜው እንደሚዘጋ ይጠብቁ። መንገዶች ከመዘጋታቸው በፊት ሠራተኞች ምልክቶች ይለጥፋሉ።

Barnes Creek ማስተካከያ ቦታ ላይ የሚኖሩ ከሆነ፥ ቀን በግንባታ ሰዓታት ላይ ከግንባታ መሣሪያ ድምጽ ይጠብቁ። አብዛኛው ሥራ የሚሠራው በእጅ መሣሪያዎች እና በአነስተኛ የግንባታ ማሽኖች ነው።

የምኖረው፥ የምሠራው ወይም የምጓዘው በኬንት ውስጥ ነው

ወደ ደቡብ ሂያጅ I-5 ከ SR 516 እና South 272nd Street መካከል

WSDOT ትራፊክ በ SR 509 እና I-5 መካከል ሲሸጋገር እንዲረዳ በ I-5 ላይ ማሻሻያዎች እያደረገ ነው በ SR 516 እና South 272nd Street መካከል አዲስ ወደ ደቡብ ወሳጅ መስመር ከSR 509 ወደ ኬንት ቫሊ እና ፌዴራል ዌይ ለሚጓዝ ትራፊክ I-5 አቅም ይጨምራል። ሠራተኞች ሥራ ይጀምራሉ ተብሎ የሚጠበቀው ክረምት 2024 ላይ ነው።

ወደ ደቡብ ወሳጅ I-5ን የሚጠቀሙ ከሆነ፥ በርካታ የጥግ መስመር መዘጋት እና በየጊዜው የማታ እና የቅዳሜና እሁድ የመስመር መዘጋቶች ይጠብቁ። ሁሉም የግንባታ ሥራ የሚካሄደው ከጊዜያዊ ሲሚንቶ ማገጃዎች ኋላ ሲሆን፥ ተጓዥ ሕዝብ ግን ሁልጊዜ በሥራ ዞኖች ሲያልፍ ዝግ ማለት እና ከሥራ ቦታዎቹ የሚገቡና የሚወጡ ጭነት መኪናዎችን ማስተዋል አለባቸው።

South 259th Street አጠገብ McSorley Creek

ከ South 272nd Street በስተሰሜን በሚገኘው በ McSorley Creek በI-5 ስር ያለ ቦይ የውሃውን ፍሰት ለመጠበቅ እና I-5ን የመቋቋም አቅም እንዲኖረው በትልቁ ቦይ ይተካል። ሠራተኞቹ የግንባታ ቦታው ጋር የሚገቡት በSouth 259th Street በኩል ነው።

South 259th Street አጠገብ የሚኖሩ ወይም በሱ በኩል የሚጓዙ ከሆነ፥ በዚህ ቦታ ላይ የግንባታ ትራፊክ እና በየጊዜው የመስመር እና የጥግ መስመር መዘጋት ይጠብቁ።

የማክሶርሊ ክሪክ ቦይ እና I-5 ረዳት መስመር አተረጓጎም

የድምጽ መከላከያ ግድግዳ ማራዘሚያ

WSDOT በኬንት ውስጥ ከ 32nd Place South በስተምስራቅ ወደ ሰሜን ያለውን የድምጽ መከላከያ ግድግዳ በ230 ጫማ ያራዝመዋል። ለዚህ የግንባታ የጊዜ ሠሌዳ ገና አልተዘጋጀም።

አዲስ የታቀደ የድምጽ ግድግዳ ከላይ እይታ።የጩኸት ግድግዳ ወደ ሰሜን አቅጣጫ I-5 መስመሮች እና በኬንት 32ኛ ቦታ ደቡብ

32nd Place South አጠገብ የታቀደው የድምጽ መከላከያ ግድግዳ ጎን ከሆነ የሚኖሩት፥ ግንባታው ከመጀመሩ በፊት የዳሰሳ ሠራተኞች እንዲያነጋግሩዎት መጠበቅ አለብዎት። በግንባታው ወቅት ሠራተኞች አፈሩን ለመጠቅጠቅ፣ ለድምፅ ግድግዳ መሠረት የሚሆን ሲሚንቶ ለማፍሰስ እና አዳዲስ የሲሚንቶ ፓነሎችን ለመቅረጽ ከባባድ መሣሪያዎች ይጠቀማሉ።

ቀጥሎ ምን አለ?

ግንባታው እየጨመረ ነው

ተቋራጫችን በ2024 በጋ በ Barnes Creek ማስተካከያ ቦታ ላይ መገንባት ጀምሯል፣ ከዛም በ South 160th Street/SR 509 መገናኛ እና በደቡብ ወሳጅ I-5፣ በSR 516 እና South 272nd Street መካከል ሥራ ቀጥሏል።
በ2025 ሠራተኞች አዲሱን SR 509 የፍጥነት መንገድ በ24th Avenue South እና በSouth 188th Street መገናኛ መካከል መገንባት ይጀምራሉ።

ከ2024 መጨረሻ በፊት ሠራተኞቻችን በፕሮጀክት ኮሪደሩ ውስጥ በማንኛውም ቦታ ሲቆፍሩ፣ እፅዋትን ሲያነሱ፥ ሲቃኙ እና በፍጆታ ላይ ሲሰሩ ማየት ይችላሉ። በግንባታ እንቅስቃሴዎች ላይ ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት ምርጡ መንገድ የ WSDOTን ማህበራዊ ሚዲያ መድረኮችን መከተል እና በሌሎች ቋንቋዎች ለሚገኘው በየሶስት ወር ለሚወጣው የእንግሊዝኛ ቋንቋ ጋዜጣችን መመዝገብ ነው

በማንኛውም ጊዜ ጥያቄ ካልዎት ቡድናችንን በ206-225-0674 ወይም በSR509Construction@wsdot.wa.gov ማግኘት ይችላሉ።

ደረጃ 2 ላይ ያልተካተተው ምንድነው?

ደረጃ 1 ሀ

የSR 509 ማጠናቀቂያ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ደረጃ በሲታክ ውስጥ አዲስ SR 99 ድልድይ ከሊንክ ቀላል ባቡር ከፍ ያለ መሪ መንገድ በታች እና ከ SR 509 መንገድ በላይ ገነባ። SR 99 ድልድይ በጁላይ 2022 ለትራፊክ ክፍት ሆነ።

ደረጃ 1 ለ

ይህ አሁን በሂደት ላይ ያለው የSR 509 ማጠናቀቂያ ፕሮጀክት፥ በI-5 እና 24th Avenue South መካከል የአዲሱን የሚያስከፍል የፍጥነት መንገድ የመጀመሪያ ማይል፥ አዳዲስ I-5 መግቢያና መውጫ መንገዶች፥ አዳዲስ መገናኛዎች፥ በI-5 ሥር አዲስ መሿለኪያ እና አዲስ South 216th Street ድልድይ ይሠራል። የፕሮጄክት ፎቶዎች እና ምስሎች በ Flickr ገጻችን እና በSR 509 የፍጥነት መንገድ መስተጋብራዊ ካርታ ላይ ይገኛሉ።

የአዲሱ የ SR 509 የፍጥነት መንገድ የመጀመሪያው ማይል እና የI-5 መገናኛዎች በSR 509 ደረጃ 1ለ ውል መሠረት ነው የሚገነቡት።የአዲሱ የ SR 509 የፍጥነት መንገድ የመጀመሪያው ማይል እና የI-5 መገናኛዎች በSR 509 ደረጃ 1ለ ውል መሠረት ነው የሚገነቡት።

የአዲሱ የ SR 509 የፍጥነት መንገድ የመጀመሪያው ማይል እና የI-5 መገናኛዎች በSR 509 ደረጃ 1ለ ውል መሠረት ነው የሚገነቡት።

የፕዩጀት ሳውንድ ጌትዌይ ፕሮግራም ምንድነው?

የPuget Sound Gateway Program በደቡብ ኪንግ ካውንቲ ውስጥ የSR 509 ማጠናቀቂያ ፕሮጄክትን እና በፒርስ ካውንቲ ውስጥ የSR 167 ማጠናቀቂያ ፕሮጄክትን ያካትታል። እነዚህ ማሻሻያዎች አንድ ላይ ሆነው የስቴቱን ትላልቅ ወደቦች በኪንግ እና ፒርስ ካውንቲዎች ውስጥ ካሉ ከቁልፍ ማከፋፈያ ማዕከሎች ጋር በማገናኘት የስቴቱን ኢኮኖሚያዊ ተወዳዳሪነት፥ በብሔራዊም ሆነ በዓለማቀፍ ደረጃ ያሳድጋሉ።

Page last updated: 13 Sep 2025, 01:48 PM